ሶዶ ሀገረ ስብከት ሚያዝያ 2/2017 ዓ/ም በሶዶ ሃገረ ስብከት አጠቃላይ የካህናትና የደናግላን በጾም ወራት የሚዘጋጅ የሱባኤ መርሐግብር ብጽዕ አቡነ ደጀኔ ህዶቶ የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በተገኙበት ተካሂዷል።
በሱባኤ ላይ በመገኘት መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉት የሶዶ ሀገር ስብከት ጳጳስ አቡነ ደጀኔ ህዶቶ እንደገለፁት ይህ ሳምንት ከወትሮው በተለይ መልክ ወደ ጌታ በመቅረብ ስቃዩን መከራውን እና ሞት ያለ አንዳች ሀጢያት ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ የሰጠበትን ማሰብ ይጠይቃል።አቡነ ደጀኔም አክለው እንደተናገሩት እኛ ካህናት ለምዕመናን ብርሃን ሆነን መገኘት አለብን በማለት አሳስበዋል።
ምዕመናን በዚህ ሳምንት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና መከራ እያሰቡ ወደ ንሰሐ እየገቡ ቤተክርስቲያን እንዲመጡ ከእኛ ይጠበቃል።
በስተመጨረሻም ሁሉም ቁምስናዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በወጣቶች ዘንድ የተለያዩ ዝግጅቶች ተዘጋጅቶ የሆሳዕና በዓል በድምቀት እንዲከበር አሳስበዋል።
Add comment
Comments